Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

learn24

Learn 24
Learn24

About Learn 24 - Amharic

ስለ

Mayor Muriel Bowserከከንቲባዋ መልዕክት

ትምህርት በማንኛውም ጊዜ፣ በማንኛውም ቦታ፣ የትም ሊከሰት እንደሚችል እናውቃለን---ለዚህም ነው የ Learn24 ሀሳብን የጀመርነው። ለብዙ ወጣቶች፣ ትምህርት ከትምህርት ቤት ቀን ውጭ በሙዚቃ ትምህርቶች፣ ስፖርቶች፣ የትምህርት ድጋፍ፣ ምክር እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ይቀጥላል። ይሁን እንጂ፣ ለተጨማሪ ክፍተኛ እድገት መሻሻል ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ይህንን የማግኘታቸው መጠን በጣም ዝቅተኛ ነው። በ Learn24፣ ከትምህርት ቤት ውጭ ፕሮግራም ጥራትን ከፍ ለማድረግ የተለያዩ አገልግሎት ሰጭዎችን፣ የህዝብ ኤጀንሲዎችን፣ አገልግሎት ሰጭዎችን፣ የንግድ ተቋማትን፣ ገንዘብ ለጋሾችን እና ትምህርት ቤቶችን ባካተተ በተባበረ ቡድን እንተካለን። በአንድነት፣ ተማሪዎችን በ Learn24 እናሳትፋለን፣ እናነቃቃለን፣ እንገፋፋለን!

- ከንቲባ ሚዩሬል ባውዘር


Learn24 በባውዘር አስተደደር ድጋፍ የተሰጠው ዲሲ ውስጥ የሚኖሩ ልጆች እና ወጣቶች ከትምህርት ቤት ቀን ውጭ ጥራት ያለው ትምህርት እና የእድገት እንቅስቃሴዎች የሚያገኙበት ከትምህርት በኋላ እና የበጋ ዕድል መረብ ነው። የአስርተ ዓመታት ጥናት እንደሚያሳየው ጥራት ባለው ከትምህርት ቤት ውጭ እና በበጋ ፕሮግራሞች አዘውትረው የሚሳተፉ ልጆች እና ወጣቶች በትምህርት ውጤታቸው፣ ማህበራዊ እና ስሜታዊ ትምህርት እና ጤናና ደህንነት ጥቅም እንደሚያገኙ ያመለክታል።

በተጨማሪም፣ ከትምህርት ቤት ውጭ (OST) ፕሮግራሞች የሚሳተፉ ወጣቶች በትምህርት ቤት ተሳትፏቸውን አሻሽሏል፤ ከፍተኛ የምረቃ ውጤቶች፣ ዝቅተኛ ከትምህርት ቤት መውጣት፤ ጠንካራ የአካዳሚ ወጤትን እና የተሻለ አዎንታዊ ጠባይ እና የሥራ ልምዶች አስገኝቷል።

Learn24 ከፍተኛ ጥራት ያላቸው OST ፕሮግራሞችን ማግኘት እና ማዳበር በሚከተሉት መንገዶች ድጋፍ ይሰጣል፣

  1. ከልጆች እና ወጣቶች ጋር የሚሠሩ አዋቂዎችን በ Institute for Youth Development በሚሰጡ ወርክሾፖች እና ኮንፈራንሶች ችሎታቸውን መገንባት።
     
  2. የፕሮግራም አቀራረጽ እና አፈጻጻምን ለማሻሻል በቀጥታ ከ OST ፕሮግራም መሪዎች እና ሠራተኞች ጋር በመከታተል፣ በመገምገም፣ እና በማሰልጠን መሥራት።
     
  3. ለሁሉም OST አገልግሎት ሰጭዎች ተጠያቂነትን ለመጨመር የጥራት ጠቃሚነትን ለቁልፍ ባለድርሻ አከአላት ማስተላለፍ።
     
  4. የልጆችን እና የወጣቶችን ውጤቶች መለካት እና ለመረቡ ረፖርት ማድረግ።

ከትምህርት ቤት ውጭ የገንዘብ ዕርዳታዎች እና የወጣቶች ውጤቶች ተቋም (Office of Out of School Time Grants and Youth Outcomes) በምክትል የትምህርት ከንቲባ ቢሮ የሚገኘው እና በከንቲባዋ ከትምህርት ቤት ውጭ የገንዘብ ዕርዳታዎች እና የወጣቶች ውጤቶች ተቋም ኮሚሽን (Commission on Out of School Time Grants and Youth Outcomes) እንዲያውቅ የሚያደርገው Learn24 መረብን ይመራል።

ራዕይ

በመላ በዲስትሪክቱ የሚኖሩ ልጆች እና ወጣቶች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ከትምህርት ቤት ውጭ ፕሮግራሞች እንዲያገኙ።

ዓላማ

Learn24 የመንግሥት ኤጀንሲዎች፣ የታቀደ የገንዘብ-ዕርዳታ፣ መረጃዎች ስብሰባና ሥልጠና የመስጠት ቅንብር፣ ለ OST አገልግሎት ሰጭዎች አቅም ግንባታ እና ቴክኒካል ዕርዳታ በመስጠት የኮሎምብያ ዲስትሪክት ወጣቶች ተመጣጣኝ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ከትምህርት ቤት ውጭ ፕሮግራሞች እንዲያገኙ ድጋፍ ይሰጣል።

የካቲት-17

ከንቲባ ባውዘር የ 2016 ከትምህርት ቤት ጊዜ ውጭ የገንዘብ ዕርዳታዎች ቢሮ (Office of Out of School Time Grants) እና የወጣቶች ውጤቶች ተቋም (Youth Outcomes Establishment) ድንጋጌን ፈረሙ።

የትምህርት ምክትል ከንቲባው (DME) ቢሮ ከትምህርት ቤት ውጭ የገንዘብ ዕርዳታዎች እና የወጣቶች ውጤቶች ተቋምን ለመመሥረት ከትምህርት ቤት ውጭ አቋቋሚ ቡድን በዩናይትድ ዌይ ሥር አቋቋሙ።

ሚያዝያ-17

የ 2016 ከትምህርት ቤት ውጭ የገንዘብ ዕርዳታዎች እና የወጣቶች ውጤቶች ተቋም (Office of Out of School Time Grants and Youth Outcomes Establishment) ድንጋጌ በሥራ ላይ ዋለ።

ሀምሌ-17

ከትምህርት ቤት ውጭ አቋቋሚ ቡድን፣ አገልግሎት ሰጭ ቡድኖችን በፕሮግራም ጥራት እና በመጨረሻም የዌካርት የወጣቾች ፕሮግራም ጥራት መገምገምያ ማዕከል የወጣቶች ፕሮግራም መገምገሚያ (Youth Program Quality Assessment (PQA)) ተብሎ በሚጠራው የወጣቶች ፕሮግርም ጥራት መገምገሚያ መሳሪያ በዲስትሪክቱ የወደፊት የ OST ፕሮግራም እንዲያገለግል ተመርጧል።

ጥቅምት 9-17

ከትምህርት ቤት ውጭ የገንዘብ ዕርዳታዎች እና የወጣቶች ውጤቶች ተቋም (The Office of Out of School Time Grants and Youth Outcomes) የመጀመሪያውን ዋና ዲሬክተር በመቅጠር በትምህርት ምክትል ከንቲባ ቢሮ ውስጥ ሥራውን ጀመረ።

የ OST ቢሮ የሙያ ሥልጠና የሆነው የወጣቶች እድገት ኢንስቲቱት (The Institute for Youth Development)፣ በኮሎምብያ ዲስትሪክት ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሥራውን ያካሂዳል።

የማህበረሰብ ድርጅቶች (CBO)፣ የዲ.ሲ. የህዝብ ትምሀርት ቤቶች (DCPS) እና የፓርክ እና መዝናኛ መምሪያን (DPR) ጨምሮ፣ ሀያ ሁለት ፕሮግራሞች ለጥራት እርገጠኛነትን እና የዌካርት የወጣቶች ፕሮግራም ጥራት ጣልቃ ገብነት ሂደትን ለሞመከር ተስማሙ።

የካቲት-18

ከንቲባ ሚዩሬል ባውዘር በትምህርት ቤት ውጭ የገንዘብ ዕርዳታዎች እና የወጣቶች ውጤቶች ተቋም (Office of Out of School Time Grants and Youth Outcomes) በመመራት Learn 24 ን በሥራ ላይ አዋሉ።

ተደራሽነት

ግላዊነት እና ደህንነት

ስለ DC.GOV

ውሎች እና ሁኔታዎች

ስልክ: (202) 727-3636 TTY: (776) 777-7776 [email protected].