ጥራት ባለው ከትምህርት-ቤት-በኋላ፣ ከትምህርት-ቤት-በፊት እና/ወይም በበጋ ፕሮግራሞች እንዲሁም ከትምህርት-ቤት-ጊዜ-ውጪ (out-of-school-time (OST) እየተባለ በሚታወቀው፤ በነዚህ ፕሮግራሞች የተመዘገቡ ልጆች እና ወጣቶች፣ ከፍተኛ በሆነ መጠን በትምህርት ገበታቸው የመገኘት (attendance)፣ የተሻለ ባሕሪይ እና በፈተና ውጤቶቻቸው እነዚህን ፕሮግራሞች ከማይካፈሉት በተሻለ ሁኔታ ከፍተኛ ውጤትን ያስመዘግባሉ። በ2014 ዓ.ም በተደረገው የወላጆች ጥናት መሠረት፣ አንዱ በOST እንዳይመዘገቡ እንቅፋት ሆኖ የተጠቀሰው፤ ከትምህርት-ቤት-በኋላ ፕሮግራሞቹ አጥጋቢ ያልሆነና ጥራት የሌለው እንክብካቤ ስለነበራቸው ነው። የLearn 24 ዓላማ በዲስትሪክቱ የሚገኙ ወጣቶች ከፍተኛ ጥራት ያለው ፕሮግራሞችን ማግኘት እንዲችሉ ማስቻል ነው።
ጥራት ያለው ከትምህርት-ቤት-በኋላ ወይም የበጋ ፕሮግራም መምረጥ በጣም አስፈላጊ ነው፤ ምክንያንቱም ደካማ የሆነ ፕሮግራም በልጅዎት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያስከትል ስለሚችል ነው።
የሚከተሉትን ለOST ፕሮግራም ጠቋሚ ምልክቶች ሊሆኑ ስለሚችሉ ይመልከቱ፡
ግልጽ የሆነ የፕሮግራም እቅዶች እና እነዚህኑ እቅዶችን የሚደግፍ እንቅስቃሴዎች
ግልጽ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታዎች
የተዋቀረ እንቅስቃሴዎችን የሚሰጥ የመርጃ ምንጮች ያለው
ለመማር፣ ክህሎቶችን ለመለማመድ፣ እና በሌሎች በርካታ እንቅስቃሴዎች፣ እንደ ሰዕል፣ ስፖርት፣ ሙዚቃ የመሳሰሉት ለመካፈል ወጣቶች ያላቸውን ጊዜ በጊዜ ሰሌዳው እንዲካተት የሚያደርግ
ዕድሜያቸው ከ5 – 17 ለሆኑ ቢያንስ ለእያንዳንዱ 15 ወጣቶች አንድ ዐዋቂን የመደበ
የቤት ሥራዎች ላይ እርዳታ የሚሰጡ የሠለጠኑ ሠራተኞች እና አስተማሪዎች፣ ካስፈለገ፤
ከወጣቶች ጋር በሚገባ የሚግባቡ ሠራተኞች
ቡድኖችን በሚገባ የሚቆጣጠሩ ሠራተኞች
ከፍተኛ ደረጃ ያለው ግምቶችን መስጠት የሚችሉ እና ወጣቶችን ማበረታታትን የሚቀጥሉ ሠራተኞች
የልጅዎን ፍላጎቶች ለማሟላት እንዲያስችል ተለዋዋጭ የሆነ በትምህርት ገበታ የመገኛ (attendance) ፖሊሲ ያለው
ተመጣጣኝ ክፍያ
ከወላጆች እና የትምህርት ቤት ሠራተኞች ጋር መሠረት የጣለ እና አስተማማኝ የሆነ ግኙነት ያለው
የOST አማራጮችን ለመፈለግ እርዳታ ካስፈለገዎ እዚህ ያግኙ።