የኮሎምቢያ ዲስትሪክት መንግሥት፣ (ዲስትሪክቱ) ተማሪዎች ብሩህ የሆነ የወደፊት ሕይወት እንዲኖራቸው ለማዘጋጀት እና ለመርዳት በትጋት ይሰራል። ይህንን ትጋቱን ለማስፈፀም፣ ዲስትሪክቱ ለልጆች እና ወጣቶች ከፍተኛ-ጥራት ያለው ከትምህርት-ቤት-ውጪ-ጊዜ ፕሮግራሞችን (out-of-school time (OST) programming) ሊሰጡ የሚችሉ ጠንካራ የሆኑ ድርጅቶችን ለመገንባት እና ለመርዳት ይፈልጋል። የገንዘብ እርዳታው፣ በምክትል ከንቲባ የትምህርት ቢሮ (Office of the Deputy Mayor for Education (DME) ውስጥ በሚገኘው፣ ከትምህርት-ቤት-ውጪ-ጊዜ፣ የገንዘብ እርዳታዎች እና የወጣቶች ውጤቶች (Out of School Time Grants and Youth Outcomes (OST Office) ቢሮ አማካኝነት ወቅታዊ በሆነው የንድፈ ሐሳብ (Proposal) መጠየቂያ ክፍት ይሆንና፣ የእርዳታ ገንዘቡ አሰጣጥም እንደ ገንዘቡ በእርገጠኝነት መገኘትና አለመገኘት ይወሰናል። የOST ቢሮዎችን በመወከል፣ በብሔራዊ ካፒታል አካባቢ (National Capital Area (United Way NCA) የሚገኘው ዩናትድ ዌይ (United Way) የገንዘብ እርዳታውን ለማስፈጸም በትብብር የሚሰራና የእርዳታ አሸናፊዎችን መምረጥ እና አስተዳደሩን የሚመራ ይሆናል። የOST ቢሮ፣ ከትምህርት-ቤት-ውጪ-ጊዜ፣ የገንዘብ እርዳታዎች እና የወጣቶች ውጤቶች ኮሚሽን (Commission on Out of School Time Grants and Youth Outcomes (OST Commission)፣ የሚሰጠውን አመራር በመከተል፣ ዓላማውን እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን እያንዳንዱን የገንዘብ እርዳታ ተወዳዳሪዎች በኃላፊነት ውሳኔ ይሰጣል።