ከትምህርት-ቤት-ውጪ-ጊዜ፣ የገንዘብ እርዳታዎች እና የወጣቶች ውጤቶች ቢሮ (Office of Out of School Time Grants and Youth Outcomes) የተመረጠው የወጣት ፕሮግራም ጥራት ግምገማ (The Youth Program Quality Assessment (PQA)®፣ እንደ ዲስትሪክቱ ማዕቀፍ ሆኖ የፕሮግራም ጥራትን ለመርዳት ከአገልግሎት ሰጪዎች ጋር በመነጋገር ይሰራል። የወጣት ፕሮግራሞችን ጥራት ለመመዘን እና የሰራተኞች የሥልጠና ፍላጎቶችን ለመጠቆም PQA፣ እውቅና አግኝቶ የተነደፈ መሣሪያ ነው። በማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ካምፖች፣ እና ወጣቶች በሚዝናኑባቸው ሌሎች ቦታዎች፣ የስራ ቦታ እና ከዐዋቂዎች ጋር በአንድነት መማሪያዎች ውስጥ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል።
PQA የሚከተሉትን ዘርፎች ይገመግማል:
ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ
ድጋፍ ሰጪ አካባቢ
የእርስ በርስ ትስስር
አሳታፊ
ወጣት-ተኮር ፖሊሲዎች እና ሙከራዎች
ለወጣቶች እና ሰራተኞች ከፍተኛ የሆነ ግምቶችን መስጠት
ማግኛ መንገዶችን
የወጣቶች እና በትምህርት ቤት ውስጥ የመገኛ ዕድሜ ላይ ያሉ (school-Age) የPQA ማስረጃን መሠረት ያደረጉ የግምገማ መሣሪያዎች ናቸው። ማስረጃዎች የሚሰበሰቡት፣ ትኩረት ባለው አስተውሎ በተመራ ክትትል እና በቃለ መጠይቅ ነው። በፕሮግራሙ ሰራተኛ እና ከውጪ በመጣ ጥልቅ እውቀት ባለው ባለሙያ አማካኝነት፤ ማስታወሻ በመያዝ፣ እና ከዚያም በመቀጠል ከፕሮግራም አስተዳዳሪዎቹ ጋር ቃለ መጠይቅ በማድረግ የፕሮግራሙን እንቅስቃሴዎች ትኩረት ባለው አስተውሎ ይከታተላሉ። ማስታወሻዎቹ፣ ትኩረት ባለው አስተውሎ የተደረገባቸው ክትትሎች፣ እና የቃለ መጠይቅ የመረጃ ስብስብ፣ ነገሮችን ነጥብ ለመስጠት እንደማስረጃ ሆነው ያገለግላሉ። የነጥቦቹ ስብስብ በአንድነት የፕሮግራሙን አጠቃላይ የጥራት ገጽታ (program quality profile) ለመፍጠር እና ማሻሻያዎችን ለማቀድ ይጠቅማሉ። ስለPQA የበለጠ ይማሩ።