የወጣት እድገት የምንለው፣ በሰው ልጆች በልጅነት እና በጉርምስና የእድገት ደረጃዎች፣ የማህበራዊ፣ ስሜታዊ፣ የማስተዋል/ምሁራዊ፣ መንፈሳዊ፣ እና አካላዊ እድገትን የሚያጠቃልል ነው።
አዎንታዊ የወጣት እድገት (Positive youth development (PYD)፣ ወጣቶችን በማህበረሰባቸው፣ ትምህርት ቤታቸው፣ ድርጅቶቻቸው፣ የዕድሜ አጋር ቡድኖቻቸው፣ እና በቤተሰቦቻቸው ውስጥ የሚያሳትፋቸው ዘዴ ሲሆን፤ ምርታማ እና ገንቢ በሆነ መልኩ፣ ወጣቶች ያላቸውን አቅምና ችሎታ እንዲጠቀሙ ለማጠናከር፣ ጥረታቸውን የሚመለከት፣ የሚጠቀም፣ እና ወጣቶችን ወደ ከፍተኛና ሙሉ የሆነ እምቅ የኃይል ደረጃቸው ላይ እንዲደርሱ የሚያበረታታ ነው። ለPYD ወጣቶች ከሚቀርቡ ሌሎች አቀረረቦች የተለየ የሚያደርገው፣ በልጆች ባህሪይ ወይም እድገት ውስጥ “ትክክል ያልሆነ”ን ነገር ለማረም ሙከራ ለማድረግ ትኩረት መስጠትን የሚቃወም በመሆኑ ነው።
የወጣት እድገት ውጤቶች፣ ልጆች እና ወጣቶች ወደሚፈልጉት የእድገት ፍላጎቶቻቸው እንዲደርሱ የተነደፉ ፕሮግራሞች እና እርዳታ መስጪያዎች ውጤቶች ነው። እነዚህ ውጤቶች በሁለት ምድቦች ተከፍለዋል:
ማንነት
ልጆች እና ወጣቶች አዎንታዊ ማንነትን የሚያሳዩት፣ የግል ደህንነት ሲሰማቸው እና ከሌሎች ጋር ተያያዥነት እና ዋስትና ሲሰማቸው ነው።
- ደህንነት እና መዋቅር
- ለግል ማንነት ዋጋ መስጠት (Self-Worth)
- የበላይነት (Mastery) እና የወደፊቱ
- ባለቤትነት (Belonging) እና አባልነት
- ሃላፊነት እና ሉዓላዊነት
- ራስን ማወቅ እና መንፈሳዊነት
ብቃት/ችሎታ
ወደ ኮሎጅ፣ የሥራ መስክ እና ለሕይወት የሚያዘጋጃቸውን እውቀት፣ ክህሎቶችን እና ባሕሪያትን ሲያገኙ፣ ልጆች እና ወጣቶች ብቃት/ችሎታቸውን ያሳያሉ።
- የሠውነት ጤንነት
- የአዕምሮ ጤንነት
- አዕምሮአዊ ብቃት
- የተቀጣሪነት አቅም (Employability)
- የዜግነት እና የማህበረሰብ ብቃት
- ባህላዊ ብቃት
- የቃላት መፍቻው (glossary) ከተጠናቀቀ በኋላ እንደገና ይስተካከላል (Update ይደረጋል)።